ያዩኛል….
ከሞዴል
ሊገዳደር አልተገነባም ሰውነቴ
ከአለም
ቆነጃጅት ተፋልሜ ዘውድ አልደደፋሁም በአናቴ
……………………………………..ግን
ያዩኛል
የቀልባቸውን
እኔ ላይ ማረፍ ምስጢር ይጠይቁኛል
እና እኔም እላቸዋለሁ….
ሞገሴ
የተንሰራፋው በጭስ የደከመ አይኔ ላይ ነው
ትክ
ብላችሁ ብታነቡት ቀለሙ ራሮት ነው
የአዘኔታ
ማጨጃ ሰፊ ማሳ ይህ አይኔ ነው
ፀሀይ
ወጥታ የምትጠልቀው እዚሁ አይኔ ላይ ነው
እነሆኝ
እንግዲህ ምስጢሬ ይሔው ነው
እላቸዋለሁ
እልና
ደግሞ…… የለም እላላሁ……የለም
…………..ይህ
ብቻማ አይደለም
የአዳምን
ህልም የፃፍኩበት መዳፌ ላይ ነው ምስጢሬ
በአፍ
በአፉ ያጎረስኩት ቁራሼ ነው ምስክሬ
እንደ
ከንአን ምድር ማርና ወተት የሚያዘንቡት
መንታ
ጡቶቼ ላይ ነው ውበቴን ያተምኩት
በአብራኬ
ክፋዮች ሽንት ነው
ታሪኬን ጀርባዬ ላይ የሳልኩት
በፀጉሬ
ጉንጉን ነው ጎተራዬን የሰራሁት
እላቸዋለሁ…..
እልና
ደግሞ…… የለም እላለሁ……የለም
ይህ
ብቻማ አይደለም………………
ታሪኬን
ታሪካችሁን በሚተርከው እርምጃዬ ነው ቀልባችሁን የገዛሁት
ሀዘኔና
ሀዘናችሁን በጻፍኩበት ገጼ ላይ ነው ልባችሁን የማረኩት
እላቸዋለሁ………
ለቀንቶ
መራመዳችሁ እኮ የኔ መጉበጥ ተከፍሏል
ለወዛችሁ
መንጨፍጨፍ ላቤ በግንባሬ ላይ ወርዷል
ለሰውነታችሁ
መደልደል አጥንቴ ተግጧል
ለፈገግታችሁ ድምቀት ጥርሶቼ
ረግፈዋል
አረማመዴም ታዲያ ይሄንኑ ያትታል
እላቸዋለሁ……..
እልና ደግሞ……የለም እላለሁ……የለም
ይህ ብቻማ አይደለም………
ከመንገዳችሁ እያስቀረ የሚገትራችሁ
ከበራፌ
እልፍ ትርጉም ውስጡ ያለው
…..
ምስጢሩ ነው ሴትነቴ…
@ @ @
No comments:
Post a Comment