እ ቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ
ያ ሰውዬ ምናለሽ ማታ
@ @
@
ሆድ ይሉት ባላንጣ ጠላት
ተፈጥሮብሽ
ውስጥሽ እያነባ ላይሽን
አሳምረሽ
በማይስቀው ጥርስሽ ስታገጪ
ቢያይሽ
አገሬው….
መች ከፋት እያለ ተጠቋቆመብሽ
አንቺም…..
ከሳት አይኑ ለመደበቅ
የጨለማ ንግስት ሆነሽ
በበልቶ ማደርና በሰው
መሆን ክብር ወፍራም ገመድ
ዳርና ዳር ተጠፍንገሽ
ግራና ቀኝ እየተናጥሽ
መወለድሽን እየረገምሽ
እናትሽን ስትወቅሺያት
የራስሽን ገላ እየተጸየፍሽ
ደካማ ነው ስትዪ ሴትነት
መለስ አድርገሽ ደግሞ
ሴትነትሽን ስትመርቂ
የተሰደሩ ጡቶችሽን ዳሌሽን
ስታደንቂ
የህልውናሽን ጠበቃ ማዕድሽን
ሚሞላውን
እራትሽን ሚያዘጋጀውን
ሴት መሆን መሆኑን ለአፍታ
ስታውቂ
አንዴ ስታለቅሺ አንድዜ
ስትስቂ
እቆምሽበት ቦታ
ሴት አዳሪ ሚልሽ ሊያድርሽ
እየመጣ
እቴ ጓደኛዬ እቴ የሎሚ
ሽታ
ያ ትልቅ ሰውዬ ምን
አለሽ ግን ማታ
@ @
@
No comments:
Post a Comment