አንደኛው…..
ድምጹን ከፍ አድርጎ ወደ አንዱ አቅጣጫ ጣቱን ‘ንደቀሰረ
ሌባ ሌባ ሌባ…………… ያዙልኝ ይለናል፤
ፖሊስ ይመስለናል፤
ሌባ የተባለው ጣት የተቀሰረበት ታምቡር በሚበጥስ
ሰማይ ጠቀስ ድምጹ
ወደ አመልካቹ እያመለከተ ሌባ ነው
ያዙልኝ…
እንዳያመልጣችሁ እያለ ይለምናል፤
ግራ ተግባተናል፤
ሁሉም ባንድ አቅጣጫ
ባንድ አይነት
እሩጫ
ጣቱን ተቀሳስሮ እርስ በርስ ሲባረር
ሲወቃቀስ ስናይ
ሌባና ፖሊሱን
በየት በኩል እንለይ፡፡
@ @ @
No comments:
Post a Comment