ገጣሚ
አይደለሁም……..
የሼክስፒር
ብዕር
የገብርዬ
ቀለም
ለኔ
አልተሰጠኝም
ቃላት
እንደውሀ
ቅኔ
እንደ ጅረት
ካንደበቴ
አይፈስም፣
ግን
እንደው ላንድ ቀን
የግጥም
ምች መቶኝ
ወይ
ገጣሚ ቡዳ መንገዴ ላይ በልቶኝ
ለመጻፍ
ብሞክር ያውም ስለ ፍቅር
የመጀመሪያው
ግጥሜ ስላንተ ይሆን ነበር
ከዛ
እጽፋለሁ… እንዲ እያልኩ ጽፋለሁ……….
………………………..አይንህ……………………..
አይንህ
እንደ ሰማይ... እንደ ጸደይ ሰማይ
..................ኮልሎ
የጠራ ነው
የቀረ
ህይወቴን ምእራፍ በምእራፍ፣ ገጽ በገጽ ሆኖ
አይንህ
ላይ ተጽፎ፣ ተጽፎ አነባለሁ
ያን
የጠራ አይንህን ትክ ብዬ ሳየው
እንዲ
እያልኩ እጽፋለሁ
አይንህን
አያለሁ፣አይንህ ወዳለሁ
እንቅልፍ
ባይረታብኝ ቀን ሙሉ አይቼህ
.......ባድር
መች ደክማለሁ
ግን
ገጣሚ አይደለሁም…
የሼክስፒር
ብዕር
የጸጋዬ ቀለም
ለኔ
አልተሰጠኝም
ቃላት
እንደውሀ
ቅኔ
እንደ ጅረት
ካንደበቴ
አይፈስም፣
ግን
እንደው ላንድ ቀን
በተኮላተፈ
ሸፋፋ አማርኛ
ለመጻፍ
ብሞክር
ያውም
ስለ ፍቅር
የመጀመሪያው
ግጥሜ ስላንተ ይሆን ነበር
ከዛ
እጽፋለሁ……እንዲ እያልኩ እጽፋለሁ
ከንፈርህ
ወይን ነው…….
ከንፈርክን
ወዳለሁ
እንኳን
ስሜህ ብቻ…..
እንደ
ድፎ ዳቦ…
እንደ
እማዬ እንጎቻ
ገምጬ
ብውጥህ መቼ ጠግብሀለሁ
ከንፈርህን
ወዳለሁ…. ከንፈርህ ማር አለው
የተራበች
ነፍሴ ጠግባ የምታድረው
አምራ
የምትደምቀው
ከከንፈርህ
ወለላ የበላሁ እንደሁ ነው
ብዬ
እጽፍላሁ…..
ከዛም
እጽፋለሁ እንዲ እያልኩ ገጥማለሁ
የልብህ
አታሞ የልቤ ድለቃ
ከቤትሆቨን
ቅኝት ከተራቀቀው ስልት
ለጆሮዬ
የሚጥም ይፈጥራል ሙዚቃ
ምታት
ያለው ጣትህ የጀርባዬን ክርክር
በስልት
በመላ አርጎ እንደ ክራር ሲያከር
ገላዬ
ይዘፍናል በማላውቀው ቋንቋ
ይመታል
አስክስታ
የጎጃም
እንቅጥቅጥ የጎንደር ድለቃ
እንዲ
ደሞ እላለሁ
ደረትህ
ሰፊ ነው
ደረትህን
ወዳለሁ
የቀን
እንግልቴን
የዕለቱን
ድካሜን
እንኳን
ተኝቼበት
ገና
ደረትህ ሳየው እረሳለሁ
ደረትህን
አያለሁ………ደረትህ ሰፊ ነው
ደረትህን
ወዳለሁ
እንኳን
ባንድ ሌሊት
በድሜዬ
ርዝመት
ዝንት
አለም ብጨፍር ብገላበጥበት
የማያልቅ
ሜዳ ነው…………ደረትህ ሰፊ ነው
ደረትህን
ወዳለሁ
ግን
ገጣሚ አይደለሁም…………………………………..
የሼክስፒር
ብዕር
የጸጋዬ
ቀለም ለኔ አልተሰጠኝም
ቃላት
እንደውሃ
ቅኔ
እንደ ጅረት ካንደበቴ አይፈስም
ግን
እንደው ላንድ ቀን
የግጥም
አማልክት ዘይት ቀብተውኝ
የቅኔዋ
አድባር ደጇን ብትከፍትልኝ
ከዛ
እኔ ደፍሬ ለመጻፍ ብሞክር
ያውም
ስለ ፍቅር
የመጀመሪያው
ግጥሜ ስላንተ ይሆን ነበር
ከዛ
እንዲ እላለሁ
ደረቴን
ነፍቼ ላ’ለም አወራለሁ
እሱ
እላለሁ………….እሱ ግጥሜ ነው
እኔ
ደግሞ ግጣሙ……………………ገጣሚው